በአውሮፓ ሃገራት ለምትኖሩ የኢትዮ ኩባ አብሮ አደግ እህቶችና ወንድሞቻችን በሙሉ:- ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ በነበረው የኮረና ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በተደጋጋሚ ቢራዘምብንም በጉጉት መጠበቃችንን ያልተውነው የማህበራችን አመታዊ ዝግጅት ከ ጁላይ 21 እስከ 24 2022 በእስፔን በማድሪድ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራ የጀመርን መሆኑን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ሲሆን እናንተም በቦታው በመገኘት ዝግጅቱን ከልዩ የልጅነት ትውስታ ጋር በጣም ተደስታችሁ እንደምታሳልፉ ሙሉ እምነታችን ነው ።
በቀጣይም ማህበሩ በዋናነት ትኩራት አድርጎ ከሚስራቸው ተግባራት መካከል ታዳጊ ህጻናትን ስለ ወላጅ ቤተሰቦቻቸው የትውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያና እንዲሁም እውቀትን ለመገብየት ከባህር ማዶ ተጉዘው ስለ አደጉበት እንደ ሁለተኛ ሀገራቸው ስለሚቆጥራት ኩባ ባህሎች፣ወጎችና ማህበራዊ እሴቶቻቸውን መቅሰም እንዲችሉ የማድረግ ስራ እንደመሆኑ መጠን ይህንን አላማ የሚያግዝ የተላያዩ ፕሮግራሞች ስለሚዘጋጁ ለዚህም የሚሆን ምቹ የሆኑ የመዝናኛና የስፖርት ቦታዎች አመቻችተን እንጠብቃችሁአለን።

ውድ አብሮ አደጎች መቼም እየተዝናኑ ቁምነገሮችንም መሥራት ያደግንበት ሃገር መገለጫወች ባህሪአት እንደመሆናቸው መጠን ከመዝናኛ ፕሮግራሞቻችን ጎን ለጎን በማህበሩ የጊዜአዊ ኮሚቴ አማካኝነት በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ስለተሰሩት ስራዎች ሪፖርት የሚቃርብ ሲሆን በመቅጠልም ቀደም ብለን በገባነው ቃል መሰረት ከውድ አባታችን ጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያም ጋር በዙምባቤ ሃገር ስለነበራቸው ቆይታ ገለጻ እንዲያደርጉ የምንጋብዛቸው ሲሆን በመጨረሻም የጊዜአዊ ኮሚቴው ካከናወኖቸው ተግዳራቶች መካከል በቀዳሚነት የምንጠቅሰው ማህበራችንን ህጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ የማድረግ ስራ ሲሆን በህገ ደንብ መሰረት በቀጣይ መህበሩን ለሁለት አመታት የሚመሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በጠቅላለ ጉባዬው አማካኝነት የምናስመርጥ ስለሆነ የእናንተ አብሮአደጎቻችን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን ።


እስካሁን ሁሉም መልካም እንዲሆን ለተከታታይ አመታቶች በውስጣችን ያዳበርነውን ገንቢ ፣ ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን በማዳበር ፣ በመመካከር እንገኛለን ለወደፊቱም አብሮ አደግ እህትና ወንድሞች እስከሆንን ድረስ አንዳችን ለአንዳችን እንደምናስፈልግ በህብረት በአንድ ላይ የወጠንነውን በጎ አላማችንን አሰባስበን በጠንካራ ሐሳብ ተደጋግፈን ለውጤት ለመብቃት ሀይላችንን አሰባስበን በቁርጠኝነት በተስፍ ተነሳስተናል እውን ለማድረግም በአንድ ላይ እንሠራለን እውቀቱም ችሎታውም አለን ። « TODA SUS FUERZA Y SABIDURIA ESTA EN LA UNION. »
አንድነታችን የጋራ ህልውናችን መሠረት ነው ፣ የአባቶቻችን የሀገርና የወገን ፍቅር ፣ ሰዕባዊነት ፣ ጀግንነት በእኛ ውስጥ ለዘላለም ህያው ሆኖ በልባችን ስለታተመ ይሀው ዘመን የማይሽረው ፣ ዘመን ተሻጋሪው አንድነታችን ቤተሰባዊ ፍቅራችን ባሳደግነው ማህበራዊ ግንኙነት እስካሁን የኢትዮ ኩባ ልጆች አብሮ አደግ ማህበር በሚል መሰባሰቢያ ጥላ ስር በመደጋገፍ እንኖራለን ።
መልካሙን ሁሉ እየተመኘንላችሁ በሠላም በማድሪድ ከተማ ለመገናኘት ያብቃን ።