ከሁሉም ነገር በላይ ሃገርና ሕዝብን አስቀድመው ለነፃነታችን ዋጋ የከፈሉት አባቶቻችን ፣ አያቶቻችን ፣ ቅድመ አያቶቻችን አርበኞች ለዘላለም እንዘክራለን
አሁን በቅርብ የተቆቆመውን « ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ » ለዚህ ታሪካዊ ማዕከል ዕርዳታ የበኩላችንን ለማድረግ በቁርጠኝነት ስንነሳሳ የአባቶቻችንን ታሪክ በማውሳት ለሃገራችን የገባነውን የቃልኪዳን አርማ በማስታወስ ነው ።
የቃል ኪዳን አርማው በውስጡ የተፃፈው እንዲህ ይላል « የአባቶቻችን የሀገር የወገን ፍቅር ፣ ቆራጥነት ፣ ጀግንነትና ወኔ በእኛም ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል »

ለዚህ ታሪካዊ መዕከል የበኩላችንን ዕርዳታ ብናደርግ ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው ብለን እናስባለን ለምን ቢባል እኛም የዚህ ታሪክ አካል ነን ብለን እናስባለን ፣ በልጅነት እድሜአችን ጀግኖች አባቶቻችን ለሀገር መስዋዕት ሆነው ካላሳዳጊ በቀረንበት ጊዜ መንግስት ውለታ ለመክፈል በማሰብ ነፃ የትምህርት እድል አግኝንተን በርትተን እንድንማርና የወደፊቶ ኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ውጥን ራዕይ በማሰብ ነው ።


ለትምህርት ወደ ኩባ የሚሄድት የጀግኖች ልጆችም በበኩላቸው በተሰጣቸው የነፃ ትምህርት በመጠቀም ተልዕኮአቸውን በሚገባ የሚወጡና የጀግኖች አባቶቻቸውንም የታጋይነት ዓርማ አንስተው ለኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብና ለውድ እናት ሃገራቸው ማናቸውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጅ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የቃልኪዳን ዓርማ በተወካዬቻቸው አማካኝነት አበርክተዋል ።
መንጌም ለወጣቶቹ ምክር በመለገስ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ። « ይህ እናንተ የተጎናፀፋችሁት ዕድል ከማንም ግለሰብ የተሰጣችሁ ገፀ በረከት ወይም ርህራሄ ሳይሆን አባቶቻችሁ ባፈሰሱት ደምና እንዲሁም የወደፊቶ ኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ውጥን ዓላማ ነው ።