ኑ ምስጋናችሁን ተቀበሉ
የገርባ አል-ነጃሺ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በጦርነቱ ምክንያት ት/ቤታቸው ተዘርፎ የትምህርት ቁሳቁሶቻቸው የመምህራን ዮኒፎርምና ትንሹ ጠመኔ ሳይቀር በአሽባሪው ወያኔ ተቃጥሎ ሁሉም ነገር ባዶ ነበር::
ከሁሉም በላይ ግን ልብን የሚሰብረው ወያኔ በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የጅምላ መቃብር በማድረግ የነገ ተስፋ በሆኑት ተማሪዎች ልጆች ላይ ጨለማ ለማልበስ የሄደበት ርቀት በታሪክ መዝገብ የተመዘገበ ጠባሳ ነው::
የኢትዮ-ኩባ እና የሕጻናት አምባ ልጆች በጋራ « ታሪካዊ ምላሽ ለእናት ሐገር ጥሪ! » በሚል መሪ ቃል ከአገር ውስጥም ከውጪ አገራትም ተሰብስበን ተባብረን አስተባብረን ወደ ተጎዱት ወገኖቻችን ያደረግነው ጉዞ ድጋፍና ማጽናናት ወገኖቻችን ከደረሰባቸው ህመም አንጻር ሲታይ ትልቅም ባይሆን ጥቂት የህሊና እረፍት ሰጥቶናል::
አርብ ሰኔ 3/2014 በሁለተኛ ዙር ያደረግነው ለት/ቤቱ አንገብጋቢ የሆኑ ቁሳቁሶችን መተካት/ማሟላት ዛሬ ሰኔ 6/2014 ለተማሪዎቹ በእጃቸው ገብቶ በአደባባይ ምስጋናቸውን መስማት ደግሞ የበለጠ አስደስቶናል::
እናት ሐገር ለሁላችንም የዋለችልንን ውለታ ለትውልድ የምንመልስበት ሌላ ታሪካዊ ዕድል እንዳጋጠመን በመቁጠር ወደፊትም ወገኖቻችንን ለመደገፍ እንትጋ::
የገርባ ከተማ ተማሪዎች ደስታና ምስጋና ለሁላችሁም ባላችሁበት ይድረሳችሁ::
የኩባ-አምባ አስተባባሪ ኮሚቴዎች
Etio Cubanos
Ethio-Cuban’s Community in Europe
አምባዎች ለሐገር-ጥሪ