አንድነታችን የጋራ ሕልውናችን መሠረት ነው ፣ አንዳችን ለአንዳችን መተሳሰባችን ቤተሰባዊ ስሜትን መጋራት ነው
በመጀመሪያ ደረጃ እኛ በልጅነት እድሜአችን ወደ ኩባ ሀገር የትምህርት ዕድል ደርሶን በሀገራችን መንግስት ፍቃድ ተልከን አብዛኞቻችን በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ተመርቀን
አብዛኞቹ በሀገር ውስጥ ሌሎቻችን በተለያየ ሀገራት በአለም ላይ እየኖርን ነው ።
እኛ በዛ ባሳደግነው ማህበራዊ ግንኙነት ፣ በአብሮ አደግነት የልጅነት መንፈስ ምክንያት በአጭር ምህፃረ ቃል « ኢትዮ ኩባኖስ » በሚል ስያሜ የምንታወቅበት መሰባሰቢያ ጥላ መስርተን በመደጋገፍ ፣ በመተሳሰብ እንኖራለን ።
እግዲህ ከዚህ ሀሳብ በመነሳት « መደራጀት ሐይል ነው በማለት በአውሮፖ አህጉር ውስጥ አንድ መሀበር መስርተን ህጋዊ ፍቃድ አግኝንተን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን ።
በተለያዩ የኤውሮፓ ሀገራት ለሚኖሩ አባላቶቻችን ማስተላለፍ የምንፈልገው መልክት ቢኖር ይሄን የጀመርነውን የተቀደሰ ዓላማ ግብ ለማድረስ የማህበራዊ ግንኙነታችንን ከመቸውም በበለጠ በማጠናከር ይሄን ዘመን የማይሽረው ዘመን ተሻጋሪዊ አንድነታችንን ለደስታም ሆነ ለችግር ጊዜ በአንድ ላይ ሆነን እየተረዳዳን በተግባር ማስቀጠል ነው ።

 በኤውሮፓ የተመሰረተው የኢትዮ ኩባኖች የአብሮ አደግ ማህበር ዓላማዉ
በመጀመሪያ ደረጃ ከልጅነት እስከ እውቀት የወረስነው ማህበራዊ ግንኙነታችን በጣም የማንነታችን መገለጫ ሆኖ እስካሁን ቀጥለናል ።
እንግዲህ አሁን ሁሉም መልካም ነው ብለናል ይሄንን ማህበራዊ ግንኙነታችንን በማጠናከር አቅም በፈቀደ መልኩ ወደ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመቀየር አቅማችንን ፣ እውቀታችንን በመጠቀም ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን በመፈለግ ሁላችንም በመተባበር መንገዳችን ቀና እንዲሆን መሠረት ጥለን ለምንፈልገው መልካም ነገር ለማድረግ ሁላችንም ልባችን ክፍት ይሁን ።

ለስኬታማ አመራር መኖር የመሀበሩ አባላቶች አስተዋፃ በጣም ከፍተኛ መሆኑን በማወቅ ሁላችንም ተሳትፎአችን የላቀ መሆን አለበት ። ለዚህም ነው አመራር ሲባል ሁሉንም አባላት ባለቤት የሚያደርገው ፣ የጋራ ጥረትም ወሳኝ የሆነው ።
በመደራጀት ውስጥ የአመራር ሚና ምንድን ነው?
ከላይ እዳብራራነው አመራር ማለትም አባላቶቹ ለወደፊት እድገት ወሳኝ አስተዋፆ አላቸው አንድ ስራ አስፈፃሚ ወይም በሀላፊነት ላይ ያሉ መሪዎች ሐላፊነታቸውን ለመወጣት ለአባላቶች የተወያዩበትን መመሪያ በማስተላለፍ አመራሩ ደግሞ (leadership collective) የሚባለው ከላይ የተሰጠውን አመራር በመቀበል የአመራር ሚናውን ይወጣል ።
ይሄን በጅምር ላይ ያለው ፣ በመመስረት ላይ ያለው የአብሮ አደግ ማህበር በአውሮፖ ግብ ለማድረስ « መደማመጥ አለብን ፣ የጋራ ጥረታችን ፣ መመካከራችን ፣ ሐሳብ መለዋወጥ ወሳኝ ነው ።
በተለይ የተላለፈልንን ስራዎች በሀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆን ፣ ቸልተኝነትን ማስወገድ አለብን ፣ ልግመኝነትን ማጥፍት አለብን ፣ ለወሰድነው ሀላፊነት ታዛዥ መሆን አለብን ለዚህ ነው ሁሉም የድርሻውን መወጣት ያለበት ፣ ለዚህ ነው አመራር ማለት ሁሉኑም አባላት የሚያቅፈው ።
ለወደፊቱ በትልቅ ለማደራጀት የምንፈልገው ማህበር በተወሰኑ አመራሮች ወይም በተወሰኑ ከልባቸው የሚጥሩ ሰዎች ግብን ሊመታ አይችልም…..

አመራር (leadership) ማለት ግንኙነት (Relationship) ነው
በዚህ ግንኙነት ዉስጥ ባለቤትነት መንፈስ መፍጠር በጣም ወሳኝ ነው (Ownership)..
የባለቤትነትን መንፈስ ማስረፆ ነው ማለትም የማህበሩን አባላቶች ባጠቃላይ ማሳተፍ፣ በሂደት ውስጥ ባለቤት ማድረግ ፣ የውሳኔ ሰጪ አካል ማድረግ ፣
የውሳኔአቸው ተጠያቂም ፣ ተሸላሚም ፣ ተመስጋኝም ማድረግ ፣ ማሕበሩንም የኔ ነው እንዲሉ ማድረግ ።
በዚህ ግንኙነት ውስጥ የመሪዎች የስራ ድርሻ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው ።
1- አቅጣጫ ማስቀመጥ የት ጋር መድረስ እንደምንፈልግ ምክንያቱም ግብ አለን ብለናል
በሚመሩ አባለቶች ፣ በሚከተሉ አባላቶች ፣ ልንደርስበት በምንፈልገው ሐሳቦች መሀከል የሚገኝ የሶስተዬሽ ግንኙነት ነው 2 – የማህበሩን አባላቶች ለአመራር ማብቃት ፣ ለተሰጣቸው ሀላፊነት ብቁ ሆነው የሚመጣውን መመሪያ በመናበብ በትክክል አስፈላጊውን ጊዜና ፕሮግራም ተሰጥቶት መወያየት ፣ ሀሳቦችን በትክክል መገምገም ።
3- ቁርጠኝነትንና ታማኝነትን በመሀበሩ አባላት ውስጥ በትክክል ማስረፆ ለዚህም ደግሞ እነያንዳንድ አባላት በንቃት መሳተፍ አለበት ፣ ሐሳብ መቀያየር አለብን ፣ በጥሩ ሁኔታ በመከተል ፣ በተሳተፎ በመከተል ፣ ግብረ መልስ በመስጠት የሚባሉትን ነገር በትክክል በመተግበር የሚቀመጠዉን አቅጣጫ በመፈፀም የከተላሉ ።

በማጠቃለያ የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ሀላፊዎችም ሆኑ አባላቶች ሐይላቸውን ፣ ችሎታቸውን ፣ ፍላጎታቸውን በማቀናጀት በዋነኛ ስራቸው ላይአተኩረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሰነስርዓት ( Discipilina) በጣም ወሳኝ ነው ።
የማህበሩ አባላቶች ባጠቃላይ ለስነ ሥርዓት ተገዢ መሆን አለባቸው ፣ የማህበራችን ህገ ደንብ ዋና መተዳደሪያ መሆኑን አውቆ በዲሲፕሊን መተግበር ይኖርበታል ።
በመጨረሻ የጥሩ እቅድ አንድ መመዘኛ በተግባር ሊተረጎም መቻሉ ነው ። ለዚህ ነው አፈፃፀም ራሱን የቻለ የእውቀት ፣ የችሎታ ዘርፋ ነው የሚባለው ።
የአባላት ልምዶች ፣ ሐሳብ አፍላቂነት ፣ ንቁ ተሳታፊነት የአንድን ማህበር የማስፈፀም አቅም ያጎለብታል ፣ ያሳድጋል ፣ ለከፍተኛ ውጤትም ያበቃል የሚባለው ።
Discipilina es la clave de una organizacion y nos conduce a resultados concretos,si todo lo que hacemos lo hacemos con DISCIPILINA el camino del exito esta bien definido,solo debemos estar en constante trabajo y sobre todos en costante busqueda de desarolllo.
ADELANTE AMIGOS ESTAMOS EN BUEN CAMINO.
TODOS LOS TRIUNFOS NACEN CUANDO NOS ATREVEMOS A COMENZAR….

 ሳምሶን ሽታዬ